“ድርቅ” እና ድርቅና

4 ሚሊዮንኮ ናት

የዓለም ኢኮኖሚና ሁኔታ እጅግ አስጊ በሆነበት በአሁኑ ወቅት እንኳ የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ መንግሥ አሁንም ቢሆን የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በ11 ከመቶ ሊያድግ እንደሚችል በእግርግጠኝነት እየገለጸ ነው። የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ዋነኛ ምሶሶ መሆኑ የሚነግርለት የግብርናው ዘርፍ የዋጋ ግሽበቱ ቀውስ ተጠቂ ከመሆኑም ሌላ ከጊዜ ጊዜ የሚመታው ድርቅ ሰለባ መሆኑ ይታወቃል። የአየር ሚዛኑ መዛባት ከተዘባው ኢኮኖሚ ፖሊሲና አስተዳደር ጋር ተደምሮ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩትን ኢትዮጵያውያንን የምግብ ተረጂ ማድረጉና ለአደጋ ማጋለጡ እየተነገረ ነው። ይሁን እንጂ የኢህአዴግ መንግሥት ድርቁን አስመልክቶ በተለያየ ጊዜ በሚሰጠው መግለጫ የአየር ሁኔታ እየተሻለ የሚሄድ መሆኑን በመግለጽ ምርትንና ኢኮኖሚውን ለማሳደግ ጠንክሮ እየሠራ መሆኑን ይገልጻል። በቅርቡም ባወጣው መግለጫ “ በክረምቱ ወቅት የሚኖረው ምቹ የአየር ሁኔታ በመጠቀም የምርቱ እድገቱን ቀጣይነት እናረጋግጣለን፣ ብሏል። “በአብዛኞቹ የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ አካባቢዎች መደበኛና አንዳንዶቹም ከመደበኛው በላይ ዝናብ የማግኘት እድሉ ከፍተኛ እንድሚሆን መረጃዎች እንደሚጠቁሙም ገልጿል። ከአገሪቱ ዓመታዊ ሰብሎች ምርት ውስጥ ከ90 ከመቶ በላይ የሚሆነው በዚህ የክረምት ወቅት በሚገኝ ዝናብ በመታገዝ የሚመረት መሆኑ እንደሚጠበቅም አስታውቋል። መንግሥት ለ2000/2001 ዓም የምርት ዘመን ከ700 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ማዳበሪያና አንድ ሚሊዮን 500ሺ ኩንታል ምርጥ ዘር ለገበሬው እያቀረበ መሆኑንም አመልክቷል። በዘንድሮው የመኸር ወቅት ከ300 ሚሊዮን ኩንታል እህል ምርት እንደሚጠብቅ ገልጿል።
ኮንሰርን የተባለው ትልቁ ዓለም አቀፍ የ እርዳታ አሰባሳቢ ድርጅት ደግሞ የድርቁን አሳሳቢነት ገልጾ አስቸኳይ እርምጃ ካልተውሰደ የ77 ዓይነት የረሀብ አደጋ ሊከሰት እንደምችል አስታውቋል።

ተቃዋሚዎችም በበኩላቸው መንግሥት እየከሰሱ ነው። የኦፊዴን ሊቀመንበር አቶ ቡልቻ ደምቀሳ ከአዲስ አድማስ ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ “መንግሥት ባሳለፍናቸው ወራት ያካሄዳቸው ድግሶች እንዳይበላሹበት በማሰብ “ የረሀብ ችግር እየገጠመኝ ነው” ብሎ በዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ለመግለጽ በፍራቱ ዛሬ ስዎች በረሀብ በመሞት ላይ ናቸው” ብለዋል። መንግሥት በቂ የምግብ ክምችት አለመያዙ ፣የበልግ አዝመራን ገና ለገና ተማምኖ ጥራጥሬ ወደ ውጭ አገር በመላኩና አርሶ አደሩ ከ እጅ ወደ አፍ በሆነ ኋላቀር የአስተራረስ ዘዴ ኩርማን መሬት እያረሰ ሰማንያ ሚሊዮን የደረሰውን የኢትዮጵያ ህዝብ ይቀልባል ብሎ በማሰቡ ዛሬም ኢትዮጵያውያን በድርቅ ህይወታቸው ማለፍ መጀመሩ መንግሥት ጥፋተኛ መሆኑን ያሳያል ብለዋል።
ዛሬ ሰዎችን እየገደለ ያለው ረሀብ መንስ ኤዎቹ መንግሥትና ተፈጥሮ ናቸው” ያሉት ዶ/ር መረራ ጉዲና ደግሞ የአበባ እርሻ አንዱ ምክናይት መሆኑን ይገልጻሉ። ከ አፄ ምኒልክ ዘመን ጀምሮ የአድ አና የበቾ፣ ጤፍ ማምረቻ የሆኑትን እንደ አምቦ፣ ቢሾፍቱ፣ ሆለታና ወሊሶ የመስመር ያሉትን አካባቢዎች በአበባ እርሻ መንግሥት ማጥለቅለቁ ለተከሰተው የምግብ እጥረት አስተዋጽ ኦ ማድረጉን ለአዲስ አድማስ ተናግረዋል። መንግሥት እና ካድሬዎቹ ድርቅ እንደሚከሰት እያወቁ ደብቀዋል ወይም ተፈጥሮ ወዴት እየሄደ እንደሆነ ለማወቅ ፍላጎትም ሆነ ሀሳቡ ስላልነበራቸው ዛሬ ይኸው ሰዎች በረሀብ መሞት ጀምረዋል ብለዋል። ከጥቂት ወራት በፊት እኛ ፓርላማ ድርቅ እየመጣ ነው፤ ሰዎች በምግብ ዋጋ ንረት እየተጎዱ ነው ስንል. ድርቅ አልገባም አርሶ አደሩ ሀብታም እየሆነ ስለሆነ የተሻለ ዋጋ ለመጠበቅ ሲል ሰብሉን ጎተራ ሞልቶ አስቀምጦ ነው። ይኽም መብቱ ነው” ተባልን በማለት ኢህ አዴግ ጭንቀቱ ዛሬ ማደር እንጂ በወራትና በዓመታት የሚመነዘር ፖሊሲ እንደሌለው መናገራቸው ተዘግቧል።

በአፍሪካ የኦክስፋም ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አበራ ቶላ ከአይፒ ኤስ ኮርስፖንደንት ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ እንደገለጹት በኢትዮጵያ ከጁላይ እስከ መሰከረም ባሉት ሶስት ወራት 3.4ሚሊዮን ሰዎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ይፈልጋሉ። ይህ አሁን የምግብ እርድታ እየተደረገላቸው ያሉትን 8 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያንን አይጨምርም። እንደ እሳቸው ገልጻ አሁን የተከሰተው ረሀብ 13.2ሚሊዮን ዜጎችን ችግር ላይ ጥሎ ከነበረው የ2003 ድርቅ ወዲህ ትልቁ ነው። ሌሎች ዓለም አቀፍ ተቋማት ደግም የተረጅውን ቁጥር ከፍ በማድረግ ወደ 6ሚሊዮን ያደርሱታል። በየአካባቢው በተለይም በደቡብና ምስራቅ ኢትዮጵያ እየተዘዋወሩ የድርቁ ሰለባ የሆኑትን ሰዎች ፎቶግራፎችና ታሪኮች እየዘገቡ ከሥፍራው የተመለከቱትን ሪፖርት ያደረጉ ዓለም አቀፍ የሚዲያ ተቋማት ብዙ ናቸው። ድርቁ አሳሳቢ ነው።

የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ግን ይህን አይቀበሉትም። በተለይ ችግሩን አግዝፈው ያጋንናሉ ያሏቸውን ዓለም አቀፍ የ እርዳት ድርጆቶች አጥብቀውና ደጋገመው በየመድረኩ በመውቀስ ላይ የሚገኙት የገጠር ሚኒስትሩና ም/ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ አዲሱ ለገሠ እርዳታ ሲይስፈልገን የሚደረግልንን ድጋ እናደንቃለን። ነገር ግን በውሸት ማስመሰያ በ እኛ ስም ገንዘስብ ለመሰብሰብ የሚደረገውን ጥረት እንቃወማለን” ብለዋል። አቶ አዲሱ ሰሞኑን ለፓርላማው በሰጡት መግልጫ “በመጋቢትና ሚያዝያ ዝናም ባለመጣሉ የተነሳ እርዳት የሚያስፈልጋቸው 4.6 ሚሊዮን ያህል ስዎችና 75ሺ ያህል ህጻናት መሆናቸውን ገልጸው ስላሉበት ሁኔታ የሚነገረው የተጋገነነ መሆኑን ተናገረዋል። “እነዚህ የሰብ አዊ እርዳታ ድርጅቶች በጣም በረሀብ የተጎዱ ህጻንት ምስል በቴሌቪዥን እያስዩ “ 6ሚሊዮን ሕፃንት የምግብ እጥረት ስለገጠማቸው ገንዘብ ካላገኙ በስተቀር የከፋ ጥፋት ያጋጥማል በማለት ለዓለም ህዝብ እየነገሩ ነው ብለዋል።
የኢህ አዴግ ባለሥልጣና ድርቁንና ያስከተለውንና የሚያስከትለውን ችግር ከመከላከል ይልቅ ቁጥርና ስሙ ላይ ሙግት የገጠሙ ይመስላሉ። ይህን ነገር ድርቅን ብለን እንጥራው ወይስ ረሀብ ፣ ችጋር እንበለው ችግር፣ ረሀብ ይባል ወይስ የምግብ እጥረት እነዚህ ከኢትዮጵያ መንግሥት ገጽታ ጋር ችግር እንዳያመጡ ስጋት የፈጠሩ ይመስላሉ። በኢትዮጵያ ግን ሁሉም ከተጠሩት ስሞች ውስጥ የሌለ ነገር የለም። ድርቅም ረሀብም ችግርም ችጋርም የምግብ እጥረትም ሁሉም ነገሮች አሉ። ቁጥር ከዜሮና ከአንድ መሆኑ ቀርቶ ከ4 ነው የሚጀመረው ካልተባለ በቀር 4 ሚሊዮን 600ሺ ቀላል ቁጥር አይደለም። ለሕዝብ ያውም በሞት አፋፍ ላይ ላለ ህዝብ ብዙ ነው። በዚያ ላይ አሁን እየተረዱ ያሉት 8 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ላይ ሲጨመር 12 ሚሊዮን መሆኑን ማስተዋልም ያስፈልጋል። (ዘኢትዮጵያ)