የቤተመንግሥቱ ጄነራል-ፍሬሰንበት

የንጉሠ ነገሥቱን ዙፋን ፣ጃንሆይ ትተውት እንደሄዱት ተነጥፎ የሚገኘው አልጋና መኝታ ቤታቸው ይህን ይመስላል። የወግ አልባሳትና ጫማዎቻቸው፣ ከነመላው የቤተመንግሥቱ ቅርሶችና ታሪኮች ጋር ዛሬም ድረስ ተጠብቀው ይገኛሉ ። ይህን ቅርስ በአደራ ጠብቀውና ተከላክለው ያቆዩት ብ/ር ጄነራል ፍሬሰንበት አምዴ ነበሩ። በቅርቡ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። ላለፉት 30 ዓመታት ቤተመንግሥትን በዋናነት ሲያስተዳድሩ ከነበሩት ጄነራል ፍሬሰንበት ህይወት ጋር አብሮ የሚጻፍ ብዙ ታሪክ አለ። ለምሳሌ እነዚህ ይገኙበታል።(ለማንበብ እዚህ ይመልከቱ)

ጸሐፊና ጋዜጠኛ ኮ/ል ጌታቸው ኃይሌ

ለአምስት ዓመታት ያህል የፖሊስና እርምጃው ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ነበሩ። ከዚያም የግል ፕሬሶች በብዛት መውጣት በጀመሩበት ዘመን የፈለግ- ጎዳናው- እውነተኛ ፍቅር- ሳላይሽ- መቅደላ- ታደለች- የፍቅር ቀን የመሳሰሉት በርካታ ጋዜጦችና መጽሔቶች አሳታሚ ሆነው ለራሳቸው ብእር ብቻ ሳይሆን ለበርካታ ጋዜጠኞችና ጸሐፊዎች የሙያ መድረክ ፈጥረዋል።
ኮ/ል ጌታቸው እንደ አጋታ ክርስቲ ዳንኤላ ስቲል ሸልደን ሲግል የመሳስሉ ደራሲዎችን መጽሐፍት ከእንግሊዝኛ ወደ አማርኛ በመተርጎም ከ65 በላይ የሚሆኑ የትርጉም ሥራዎችን አስነብበዋል። ከነዚህ በተጨማሪ የበርካታ ብእር ስሞች ባለቤት የሆኑት ታዋቂው ጸሐፊና ተርጓሚ ሌ/ኮሎኔል ጌታቸው መኮንን አርፈዋል። እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር መስከረም 2/2001 በ59 ዓመታቸው ባደረባቸው ህመም ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት ሌ/ኮሎኔል ጌታቸው መኮንን ባለትዳርና የ3ልጆች አባት ነበሩ። ( ሙሉውን ለማንበብ)

መላከ ገነት ውቡ

በዋሽንግተን ዲሲ የመጀመሪያው ቤክተክርስቲያን ካህንና መስራች በመሆን 27 ዓመታት ያህል ያገልገሉት መንፈሳዊው አዛውንት መላካ ገነት ውቡ እግዚአብሔርን ባከበሩበት ቤት ክብርን ከምእመናን አግኝተዋል። ሥርዓተ ክብሩ የተካሄደው ጁላይ 16/2006 ቀን በደብረ ገነት መድኃኒዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ነው። ሥነ ሥርዓቱየተከበሩ አባታችን ላለፈው እናመስግንዎታለን ቀሪውን ደግሞ ለቀሪው ህይወትዎ ሳይጨነቁ የሚኖሩበትን እንክብካቤ እናንደርግልዎታለንየሚል ይዘት ነበረው። ካህኑም በኢትዮጵያ አቆጣጠር 1976-1998 ድረስ ላበረክቱት አገልግሎት የመታሰቢያ ሽልማት በቤተክርሲያኒቱ ቦርድ ተሰጥቷቸዋል። ብዙ ምስክርነቶችም ተሰምተዋል። (ሙሉውን ለማንበብ)