ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከእስር ተለቀቀ

https://www.bbc.com/amharic/41627680

  • 15 ኦክተውበር 2017

ተመስገን ደሳለኝImage copyright
TARIKU

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከእስር ተለቀቀ።

የተዛባ መረጃን በማሰራጨትና ሕዝብን በመንግሥት ላይ በማነሳሳት ተከሶ የ3 ዓመት እስር የተፈረደበት ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከእስር ቤት ወጥቷል፡፡

አርብ ዕለት የእስር ጊዜውን ጨርሶ እንደሚፈታ ሲጠበቅ የነበረው ተመስገን ደሳለኝ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ እንደማይፈታ ከዝዋይ ማረሚያ ቤት አስተዳደር ተነግሮት ለተጨማሪ ቀን እስር ቤት ቆይቷል።

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከዚህ በፊት በአመክሮ ይፈታል ተብሎ ቢጠበቅም የተፈረደበትን የሦስት ዓመታት እስር አጠናቆ ነው የተፈታው።

ተመስገን በማረሚያ ቤት ቆይታው በወገቡና በአንድ ጆሮው ላይ የጤና መታወክና ስቃይ አጋጥሞት እንደነበር ቤተሰቦቹ ይናገራሉ።

ባለፈው ዓመት ኅዳር ወር ማብቂያ ላይ ተመስገን በዝዋይ ማረሚያ ቤት ውስጥ እንደሌለ ለቤተሰቦቹ ተነግሯቸው ከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ገብተው እንደነበር የሚታወስ ሲሆን ከቀናት ፍለጋ በኋላ ግን እዚያው ማረሚያ ቤት እንዳለ ታውቋል።

ተመስገን በጋዜጣና በመፅሔት ባለቤትነትና ዋና አዘጋጅነት በቆየባቸው ጊዜያት መንግሥትን በሚተቹ ጽሁፎቹ ይታወቃል። በተደጋጋሚ ጊዜያት የህትመት ሥራዎቹ እንዲቋረጡ ተደርግዋል።

Read more