የኦህዴድ ማእከላዊ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ነው

 

የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) ማእከላዊ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን በማካሄድ ላይ።

በአዳማ ከተማ እያካሄደ በላው ስብሰባው የኦሮሚያ ክልል ወቅታዊ ሁኔታን ጨምሮ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል።

ከዚህ ቀደም የነበረውን የድርጅቱን አሰራር እና አካሄድ የሚቀይር አዲስ አደረጃጀት እና አሰራር ላይ ምርመራ ማካሄድና የክልሉ ህዝብ ጥቅም እና ፍላጎት ላይ ትኩረት ያደረገ መሆኑም ተገልጿል።

በትናንትናው እለት በአዳማ ከተማ የተጀመረው የኦህዴድ ማእከላዊ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባ በዛሬው እለትም ቀጥሎ በመካሄድ ላይ ሲሆን፥ የተለያዩ ውሳኔዎችን አንደሚያሳልፍም እየተጠበቀ ነው።

ከነገው እለት ጀምሮም 7ኛው የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) ድርጅታዊ ኮንፍረንስ ከ2 ሺህ በላይ አባላትን በማሳተፍ መካሄድ እንደሚጀምርም ተገልጿል (ኤፍ.ቢ.ሲ) ።