አቶ በቀለ ገርባ ዛሬ ከእስር ሊወጡ ይችላሉ

https://www.bbc.com/amharic/news-41802022

  • 30 ኦክተውበር 2017

አቶ በቀለ ገርባ በ30ሺ ብር ዋስትና ከእሰር እንዲወጡ መወሰኑን ጠበቃቸው ተናገሩ።

አቶ በቀለ ገርባ በ30ሺ ብር ዋስትና ከእሰር እንዲለቀቁ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት መወሰኑን የአቶ በቀለ ጠበቃ አብዱልጀባር ሁሴን ለቢቢሲ ተናግረዋል።

አቶ አብዱልጀባር እንደተናገሩት ፍርድ ቤቱ ብይኑን የሰጠው ዛሬ ጠዋት ሲሆን፤ ”የአቶ በቀለ ገርባ ቤተሰቦች የተጠየቀውን ገንዘብ ሲፒኦ እያሰሩ ነው። የተለየ ነገር ከልተፈጠረ በቀር አቶ በቀለ ዛሬ ይፈታሉ ብለን እንጠብቃለን” ሲሉ ተናግረዋል።

ባሳለፈነው ነሃሴ ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ የዋስ መብታቸውን ውድቅ ማድረጉ ይታወሳል።

ከዘጠኝ ዓመት በፊትም 8 ዓመት ተፈረዶባቸው ከሶስት ዓመት የእስር ቆይታ በኋላ ነበር የተፈቱት።

አቶ በቀለ ገርባ ህዳር 2008 ነበር በድጋሚ ተይዘው የታሰሩት።

Read more