ፕሪሚየር ሊጉ በአሃዝ፡ ማንቸስተር ሲቲ፣ ጆሴ ሞውሪንሆ፣ ሳኤድ ኮላስኒች፣ ጂዮርጂኒዮ ዊናልደም

https://www.bbc.com/amharic/news-41800165

ፕሪሚየር ሊጉ በአሃዝ፡ ማንቸስተር ሲቲ፣ ጆሴ ሞውሪንሆ፣ ሳኤድ ኮላስኒች፣ ጂዮርጂኒዮ ዊናልደም

  • 30 ኦክተውበር 2017

ማንችስተር ሲቲImage copyright
PA

አጭር የምስል መግለጫ

ሲቲዎች በአምስት የነጥብ ልዩነት የፕሪሚየር ሊጉ ሰንጠረዥ አናት ላይ ተቀምጠዋል።

ማንቸስተር ሲቲ በፕሪሚየር ሊጉ ምርጡን አጀማመር አድርጓል፤ የአርሴናሉ ያልታሰበው ጨዋታ አቀጣጣይ

ቅዳሜ ከተደረጉ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች መካከል 10ሩ ምርጥ አሃዞች የሚከተሉት ናቸው፡

1. ማንቸስተር ሲቲዎች ዌስት ብሮምን 3 ለ 2 ካሸነፉ በኋላ፤ በአስር ጨዋታዎች ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡበት ውድድር ዓመት ሆኗል። ከአስር ጨዋታዎች ዘጠኙን በማሸነፍ በአንዱ አቻ ወጥተው 28 ነጥቦችን ሰብስበዋል።

2. ሲቲዎች በሁሉም መድረክ በ21 ጨዋታዎች ሽንፈትን አላስተናገዱም። በታሪካቸው ረዥሙ ሽንፈት ያላስተናገዱበት የጨዋታ ጊዜ ነው።

3. የፔፕ ጋርዲዮላ ቡድን ያለፉትን ስምንት ጨዋታዎች በአጠቃላይ 32 ለ 5 በሆነ የግብ ልዩነት ነው ያሸነፈው።

4. ማንቸስተር ዩናይትዶች ቶተንሃምን 1 ለ 0 ያሸነፉበት ጨዋታ ከ2007/08 ውድድር ዓመት በኋላ በሜዳቸው ባደረጓቸው አምስት ጨዋታዎች ጎል ያላስተናገዱበት ሆኗል።

5. አርሴናሎች ስዋንሲን 2 ለ 1 ባሸነፉበት ጨዋታ አንድ ጎል አስቆጥሮ እንዲሁም ለጎል አመቻችቶ ያቀበለው ሳኤድ ኮላስኒች በዘንድሮው ዓመት ከቡድኑ ተጫዋቾች ጎል በሆኑ ኳሶች ላይ ተሳትፎ በማድረግ ቀዳሚ ሆኗል። ሶስት ጎሎችን አስቆጥሮ ሶስት ለጎል የሚሆኑ ኳሶችን ደግሞ አመቻችቶ አቀብሏል።

6. ስዋንሲ በዘንድሮው ዓመት ወደ ጎል በተሞከሩ ኳሶች (76) እና ዒላማቸውን በጠበቁ (20) ኳሶች ዝቅተኛውን ደረጃ ይዟል።

7. በዘንድሮው ዓመት ከአምስቱ ታላላቅ የአውሮፓ ሊጎች በሁሉም ጨዋታዎች ጎል የተቆጠረባቸው ክለቦች ክሪስታል ፓላስ፣ ቤኔቬንቶ፣ ማላጋ እና ዲዮን ናቸው።

8. ዌስትሃምና ክሪስታል ፓላስ አቻ በወጡበት ጨዋታ ጃቪየር ሄርናንዴዝ 41ኛ የፕሪሚየር ሊግ ጎሉን አስቆጥሯል። ሁሉም ጎሎቹ ከግብ ክልል ውስጥ የተገኙ ናቸው። የቀድሞው የኤቨርተን ተጨዋች ቲም ካሂል ብቻ ነው ሁሉንም 56 ጎሎቹን ከግብ ክልል ውስጥ በማስቆጠር የሚቀድመው።

9. የሊቨርፑሉ አማካይ ጂዮርጂኒዮ ዊንናልደም ቡድኑ ሃደርስፊልድን 3 ለ 0 ባሸነፈበት ጨዋታ 18ኛ የፕሪሚየር ሊግ ጎሉን አስቆጥሯል። አስራ አንዱን ለኒውካስል ያስቆጠረ ሲሆን ቀሪዎቹን ደግሞ በሊቨርፑል ያስቆጠራቸው ናቸው። ተጫዋቹ ሁሉንም ጎሎች ያስቆጠረው በክለቦቹ ሜዳ ሲሆን በዚህም ቀዳሚው ተጫዋች ነው።

10. ዋትፎርድ በዚህ ሳምንት በስቶክ 1 ለ 0 ተሸንፏል። ባለፈው ሳምንት በቼልሲ መሸነፉን ተከትሎ በዚህ ዓመት በተከታታይ የተሸነፈበት ጨዋታ ሆኗል።

Read more