የጥቅምት ወር የዋጋ ግሽበት ወደ 12 ነጥብ 2 በመቶ ከፍ አለ

የጥቅምት ወር አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 12 ነጥብ 2 በመቶ ሆኖ መመዝገቡን የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ ገለፀ።

ኤጀንሲው በያዝነው ወር የእህል ዓይነቶች መረጋጋት የታየበት ቢሆንም የፍራፍሬ በተለይም ሙዝ፣ ስኳር እና ቡና ዋጋ በጥቅምት ወር ዋጋቸው ጨምሯል። የቲማቲምና የካሮት ዋጋ ከተጠበቀው በላይ ጭማሪ አሳይቷል።

በአጠቃላይ ካለፈው ወር ጋር ሲነፃጸር በዚህ ወር የእህልና የጥራጥሬ ዋጋ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃጸር ግን የዋጋ ግሽበቱ ከፍ ማለቱን ኤጀንሲው ያስታወቀው።

የመስከረም ወር የዋጋ ግሽበት 10 ነጥብ 8 በመቶ ሆኖ መመዝገቡ ይታወሳል። (ፋና)