ጠ/ሚ ኃ/ማርያም ፡ በአል አሙዲ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ላይ እክል ይፈጠራል ብሎ መንግስት አያምንም

 

ሳዑዲ አረቢያ ከሙስና ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር ካዋለቻቸው ግለሰቦች መካከል አንዱ የሆኑት ትውልደ ኢትዮጵያዊው ቢሊየነር የሼክ መሀመድ ሁሴን አሊ አል አሙዲንን በተመለከተ መንግስት በዲፕሎማሲያዊ መልኩ ጉዳዩን አስመልክቶ መረጃን እየተከታተለ መሆኑን ተናገሩ
በኢትዮጵያ ባለው የእሳቸው ኢንቨስትመንት ላይ እክል ይፈጠራል ብሎ መንግስት እንደማያምንና ሳዑዲ አረቢያ ሉዓላዊ ሀገር እንደመሆኗ ከኢትዮጵያ መንግስት በኩል ሌላ ሊሰራ የሚችል ምንም ነገር አለመኖሩን ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሰሞኑን ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ በአገሪቱ የውስጥ ጉዳዮች ችግር ላይ ሁሉም የኢህ አዴግ ድርጅቶች ችግር ያለባቸው መሆኑን ተናግረዋል።
በየትኛውም አካባቢ ያለ ህዝብ የእኔ ህዝብ ነው ብሎ ያለማሰብ የአቋም ችግር የሁሉም የኢህአዴግ አባል እና አጋር ድርጅቶች ችግር መሆኑን ነው አስረድተዋል።
የፌደራል እና የክልል የፀጥታ አካላት በተቀናጀ ሁኔታ ያለአግባብ መጠቀም የሚፈልፈጉ አካላትን ከዚህ ድርጊታቸው ለማስቆም እና በዘላቂነት ይህን ድርጊት ለማጥፋት እንዲሁም ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን ከዚህ ሳምንት ጀምሮ የኢትዮጵያ ብሄራዊ የደህንነት ምክር ቤት ስራ መጀመሩን አንስተዋል።
የፀጥታ አካላት ማስከበር ያለባቸውን ህገመንግስቱን እና ህገመንግስታዊ ስርዓቱን ሆኖ ሳለ ጥቂት የፀጥታ አካላት በደም እና በጎሳ ለይቶ ህዝብን የማየት አዝማሚያ እንደተስተዋለባቸው ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ አንዳንድ የፀጥታ አካላት በግጭት ውስጥ ተሳትፈው በመገኘታቸው እርምጃ ተወስዶባቸዋል ብለዋል (ተጨማሪ )