ደብረጽዮን ገብረሚካኤል የህወሓት ሊቀ መንበር ሆነው ተመርጠዋል

የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ ከአንድ ወር በላይ ሲያካሂድ የነበረውን ግምገማ ማጠናቀቁን ገለፀ። ዘጠኝ አባላት ያሉት የድርጅቱን ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ምርጫም አካሂዷል።

በዚህም መሰረት፦

ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል የድርጅቱ ሊቀ መንበር

ወይዘሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሄር-ምክትል ሊቀ መንበር

አቶ ጌታቸው አሰፋ

አቶ አለም ገብረዋህድ

ዶክተር አዲስአለም ባሌማ

አቶ አስመላሽ ወልደስላሴ

አቶ ጌታቸው ረዳ

ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም እና

ዶክተር አብርሃም ተከስተ

የህወሓት ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ተደርገው ተመርጠዋል።