ዶናልድ ትረምፕ ጁኒየር ለዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት የሥለላ ኮሚቴ ዝግ ሸንጎ ቃላቸውን ይሰጣሉ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ ልጅ ዶናልድ ትረምፕ ጁኒየር ዛሬ ለዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት የሥለላ ኮሚቴ ዝግ ሸንጎ ቃላቸውን ይሰጣሉ። ምክር ቤቱ በአምናው የሀገሪቱ ምርጫ የሩስያ ጣልቃ ገብነት ዙሪያ ምርመራውን ቀጥሏል።