ዶ/ር አብይ የኢህአዴግ ሊቀመንበር አቶ ደመቀ ም/ሊቀመንበር ሆነው በድጋሚ ተመረጡ


ሶስት አባላት ያሉት የቁጥጥር ኮሚሽን አመራር ምርጫም ተካሂዷል።

የኢህአዴግ 11ኛው ድርጅታዊ ጉባኤው ዛሬ በማጠናቀቂያ ቀኑ የግንባሩን ሊቀመንበር እና ምክትል ሊቀመንበር ምርጫ አድርጓል።
በዚህም መሰረት ዶክተር አብይ አህመድ የግንባሩ ሊቀመንበር አቶ ደመቀ መኮንን ደግሞ ምክትል ሊቀመንበር በመሆን በድጋሚ ተመርጠዋል።
ዛሬ በተካሄደው ምርጫ 177 ሰዎች ድምጽ የሰጡ ሲሆን ዶክተር አብይ 176 ድምጽ በማግኘት ሊቀ መንበር በመሆን ተመርጠዋል።
ለምክትልነት በተሰጠው ድምጽ ደግሞ አቶ ደመቀ መኮንን 149 ድምጽ በማግኘት ምክትል ሊቀ መንበር ሆነው በድጋሚ ተመርጠዋል።

በኢህአዴግ ቁጥጥር ኮሚሽን አመራሮች ምርጫ
ኢንጅነር አወቀ ሀይለማርያም – ከአዴፓ ሰብሳቢ
አቶ ጀማል ረዲ – ከደኢህዴን ምክትል ሰብሳቢ እንዲሁም
አቶ ብርሃኑ ፈይሳ ከኦዴፓ ፀሀፊ ሆነው ተመርጠዋል።
ተመራጮቹ ለቀጣዮቹ ሁለት አመታት የድርጅቱን የቁጥጥር ኮሚሽን የሚመሩ ይሆናል።