መንግሥት ተማሪዎችን ሊመግብ ነው

መንግስት በአዲስ አበባ ለሚገኙ ሁሉም የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች ቁርስና ምሳ እንደሚያቀርብ ማስታወቁን ኢትዮ ኤፍ ኤም ዘግቧል።
የከተማ አሥተዳደድሩ ትምህርት ቢሮ እንደገለጸው በመንግስት ትምህርት ቤቶች ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎችን በሙሉ ለመመገብ መርሃ ግብር ተይዟል።
የትምህርት ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ሃለፊ አቶ አበበ ቸርነት የምገባ መርሃ ግብሩ ታቅዶ እየተሰራበት ነው፤ ተማሪዎች የ 2012 ዘመን ትምህርታቸውን ሲጀምሩ ይጀመራል ብለዋል፡፡
“ማንም ተማሪ ሆዱ ባዶ ሀኖ ትምህርት ገበታ ላይ መቀመጥ የለበትም የሚለውን ታሳቢ ያደረገ መርሃ ግብር” እንደሆነም ገልጸዋል።
ከዚህ ቀደም እንዲህ በስፋት ባይሆንም የተለያዩ በጎ አድራጎት ድርጅቶች የመንግስት ትምህርት ቤት ተማሪዎችን ይመግቡ ስለነበር ልምዱ ስላለ ምገባው አስቸጋሪ እንደማይሆንም አስረድተዋል።
ከተማ አስተዳደሩ ምገባ ብቻ ሳይሆን በአዲስ አበባ ለሚገኙ አጠቃላይ ተማሪዎች የደንብ ልብሳቸውንና የትምህርት ቁሳቁሳቸውንም እንደሚችል አሳውቋል፡፡
የትምህርት አከባቢውን ለመማር ማስተማር ሂደቱ ምቹ ለማድረግና አዲስ መንፈስ ለመፍጠርም 488 ትምህርት ቤቶች መታደሳቸውንም አቶ አበበ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡
ከዚህ ቀደም ከተለያዩ ድጋፍ ሰጪ አካላት ከ7 ሚሊዩን በላይ ደብተር እንደተሰበሰበ መገለፁ የሚታወስ ሲሆን
በ2011 ትምህርት ዘመን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር በአጠቃላይ 918 ሺህ 207 ተማሪዎች እንደነበሩም ተዘግቧል።